መጋቢት 13/2010 ዓ.ም

ለትምህር ፈላጊዎች

ጉዳዩ፡   የሴቶች ማደሪያ (ዶርሚቶሪ) ማለቁን ማሳወቅና የተማሪዎን ቅበላ ይመለከታል፡-

አስቀድመን በጌታችንና በመድሐኒታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ስም የከበረ ሰላምታችንን እናቀርባለን፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በተለይም ሴቶች እህቶቻችን በአመራር/ በአገልግሎት እንዲሳተፉ ውሳኔ ካስተላለፈችበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ከወንዶች ጋር ሆነው በጌታ ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማበረታታት ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ኮሌጃችንም የቤተ ክርስቲያናችንን ውሰኔ ግምት ውስጥ በማስገባት ሴት እህቶቻችን ወደ ኮሌጁ ገብተው እንዲማሩ በየጊዜው ጥረት ሲያደረግ የቆየ ቢሆንም በኮሌጁ ያለው ጊዜያዊ የሴቶች ማደሪያ ቦታ እንደ ወንዶች ማደሪያ ቦታ ምቹና በቂ አለመሆኑን በመገንዘብ  ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት ባቀረበው ፖሮፖዛል መሰረት በተገኘው የገንዘብ ድጋፍ  ከ2 ዓመት በፊት የተጀመረው 258 ሴቶችን የሚይዝ G+3 ህንፃ ግንባታ  በአሁኑ ስዓት በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን እስከ ግንቦት አጋማሽ ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል፡፡

ስለሆነም በ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተዘጋጀው ዶርም/ ማደሪያ ሴቶች አገልጋዮቻችን ልክ እንደ ወንድሞቻቸው በሰፊው ወደ ኮሌጃችን ገብተው በመማር ተጠቃሚዎችና ጠቃሚዎች እንዲሆኑ ለማስቻል ከወዲሁ በተለያዩ አካላት ተገቢው ሁሉ እንዲፈፀም  ይህንኑ  በቤተክርስቲያናችን ስር ላሉት የመሰረተ ክርስቶስ ክልል ጽ/ቤቶች ከወዲሁ መረጃ መስጠቱ አስፈላጊ ሁኖ አግኝተነዋል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያም ሆነ በቀሪው  ዓለም የቤተ ክርስቲያንን ዓላማና ተልዕኮ ተፈጻሚ ለማድረግ ኮሌጁ የሚያደርገው ጥረት የበለጠ እውን እንዲሆን ለማስቻል በየክልሎቻችሁ ያሉትን የመሰረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትንና ሌሎች ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት የሚያገለግሉ የሙሉ ጊዜ አገልጋዬች/ጾታ ሳይለይ/ና ለወደፊቱ አገልጋይ ሊሆኑ የሚችሉ እህቶችና ወንድሞች በዲግሪ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ በሥነመለኮት ትምህርት ፕሮግራሞች  ወደ ኮሌጃችን በመግባት መማር እንደሚችሉ በእናንተ በኩል በደብዳቤ፤ በአካልና በሌሎች መንገዶች  ከወዲሁ እንዲገለጽላቸው ስንጠይቅ ለሚደረግልን ቀና ትብብር ከወዲሁ ጌታ ይባርካችሁ ማለት እንወዳላን፡፡

 

መሠረተ ክርስቶስ ኮሌጅ